Thursday, November 22, 2012

ህዳር 14



ህዳር 14

በዚህች ቀን አባ ዳንኤል አረፈ፤ የዚህን ቅዱስ አባት ታሪኩን ለማንበብ ስንክሳሩን ሲገልጡ አንድ የሚያስገርም ታሪክ ይገኛል፤ ታሪኩ እንዲህ ነው በዘመኑ የነበረው የፋርስ ንጉስ ጽኑ በሆነ የሆድ በሽታ ይሰቃይ ነበር ባለመድሐኒትም ሊፈውሰው አልቻለም፤ከንጉሱ ማዕድ የሚመገብ አንደ አስማተኛ ነበር ንጉሱ አስጠርቶ ስታመም ካላዳንከኝ ከኔ ጋር መኖርህ ጥቅሙ ምንድ ነው ካልፈወስከኝ እገድልሃለው ይለዋል፤ይህም አስማተኛ ማምለጫ ፈልጎ ንጉስ ሆይ የምነግርህን ስማኝ ለእናትና አባቱ አንድ ብቻ የሆነ ልጅ አስመጣ እናቱ አስራ ትያዘው አባቱም ይረደው በእርሱም ደም ትድናለህ ይለዋል፤ እንደተባለውም 1000 የወርቅ... ዲናር ልጅ እንዲገዙለት አሽከሮቹን ይልካል፤ አንድያ ልጅ ያላቸው ድሆች ተገኙ 1000 የወርቅ ዲናር ልጃቸውን ሊያርዱ ተስማሙ፤ ህጻኑ ግን እያለቀሰ እንዲህ አለ እኔ እግዚያብሔር እንደሚያድነኝ አምናለሁ አላቸው፤ እናቱ አጥብቃ አሰረችው አባቱ ደግሞ ሊያርደው ሾተሉን አነሳ፤ ህጻኑ አይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ ከንፈሩን እያንቀሳቀሰ ጸለየ፤ እግዚያብሔር በንጉሱ ልብ ርህራሄ አሳደረ፤በቃ ልቀቁት ፍቱት ብሎም አዘዘ፤ ህጻኑንም ጠርቶት ወደ ሰማይ እየተመለከትክ ምን አልክ አለው፤ ህጻኑም ጌታዬ ሆይ ልጅን የሚገፋው ቢኖር እናት አባቱ ያድኑታል፤ እናት አባቱ ቢገፉት ንጉስ ዳኛ ሆኖ ያድነዋል፤እኔን ግን እናቴም አባቴም ንጉሱም ጨከኑቢኝ እንተ ብቻ ነው ያለከኝ እግዚያብሔር ሆይ እርዳኝ ብዬ ነው የጸለይኩት አለው፤ንጉሱ ተደነቀ እራራለትም 1000 የወርቅ ዲናር ሰጥቶ አሰናበተው፤ ከዚህ በኃላ ነው የዛሬውን ቀን መታሰቢያ የምናደርግለት አባ ዳንኤል ወደ ንጉሱ ከእግዚያብሔር ታዞ የመጣው ንጉሱን ከደዌው ፈወሰው ወንጌልንም ሰብኮ በክርስቶስ እንዲያምን አደረገው ከነቤተሶቹም አጠመቀው፤ወደ ገዳሙ ተመልሶ በቅድስና በተጋድሎ ኖሮ በዛሬዋ ቀን አረፈ። በረከቱ ይደርብን።

No comments:

Post a Comment