Tuesday, November 13, 2012

ህዳር 3



 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ህዳር

በዚህች ቀን ጻድቁ ንጉስ ነአኩቶ ለአብ አረፈ፤ ይህ ጻድቅ የቅዱስ ላሊበላ የወንድም ልጅ ነው አባቱ ሐርበይ እናቱ መርኬዛ ይባላሉ፤ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ ክህነትን ከንግስና ይዘው ኢትዮጰያን ከመሩ አራቱ የዛጌ ነገስታት አንዱ ነው፤ ቤተክርስቲያን ለነዚህ አራት ነገስታት ጽላት ቀርጻላቸው ቤተክርስቲያን አንጻላቸው የቅድስና ስም ሰጥታቸው ታከብራቸዋለች፤ ይምርሃነ ክርስቶስ፤ላሊበላ ነአኩቶ ለአብና ገብረ ማርያም ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ በነገሰበት 40 ዓመት ሙሉ አርብ አርብ ቀን የጌታን ህማም እያሰበ በዘውዱ ፋንታ የእሾህ አክሊል ደፍቶ፤5 ጦር ዙሪያውን ተክሎ እየደማ እያለቀሰ ሲጸልይ ሲሰግድ ይውል ነበር፤ከእለታት በአንዱ ቀን ጌታችን ተገለጸለት እንዲህም አለው ወዳጄ ነአኩቶ ለአብ እኔ ለዓለም ደሜን ያፈሰስኩት አንድ ቀን ነው፤ አንተ ግን 40 ዓመት ሙሉ ደምህንንና እንባህን ስታፈስ ኖርክ ይበቃሃል አሁን ወደ እኔ ልወስድህ ነው ይለዋል፤ነአኩቶ ለአብም ጌታችንንጌታዬ ሆይ እዚህ ቦታ እኔን ብለው የሚመጡ ወገኖቼን ማርልኝ ይለዋልጌታም እውነት እልሃለው ቦታህን ባይረግጥ ዝክርህን ባያዘክር እንኳን ዝናህን ሰምቶ ያሰበህን ኃጢያቱ ምን ቢበዛ እምርልሃለው፤ ዳግመኛም እልሃለው 40 ዓመት ሙሉ እንባህን ያፈሰስክባት ይህች ድንጋይ እስከ እለተ ምጽአት እያነባች ትኖራለች ከዚህ ለሚጠጡ ለሚጠመቁ ድህነት ይሁናቸው ብሎታል፤ ዛሬም ድረስ የነአኩቶ ለአብ ቤተክርስቲያኑ ባለበት ከጣራው ስር ጻበሉ እየቆየ ጠብ ጠብ ይላል፤ክረምት ከበጋ እይለይም እንዲያውም በበጋ መጠኑ ይጨምራል ይህ ጸበል እጅግ መድሐኒት ነው፡፡ ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አሸተን ማርያምን አንጾ ከጨረሰ በኃላ ማዕጠንት ይዞ ቤተክርስቲያኑን ሲያጥን ብዙ ቅዱሳን እጣኑን አሽትተው ቤተክርስቲያን ውስጥ ጥቅጥቅ ብለው ቆሙ፤ እናንተ ደግሞ እንዴት መጣችሁ አላቸው እነርሱም እጣኑን አሽትተን መጣን አሉት በዚህም የተነሳአሸተን ማርያምተብላለች፤ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ 70 ዓመቱ ህዳር 3 ቀን እንደነ ሄኖክ ተሰውሯል። በረከቱ ይደርብን፡፡  

ምንጭ የይምርሃነ ክርስቶስና የነአኩቶ ለአብ ገድል


No comments:

Post a Comment