Thursday, February 21, 2013

ጥር 29


በዚህች ቀን የከበረች ቅድስት አክሳኒ አረፈች። ከሮም ከነገስታት ወገን ነች ወላጆቿ በሀብት በዘመድ የከበሩ ነበሩ፤ ከእርሷ ሌላ ግን ልጅ አልነበራቸውም፤ይህች ቅድስት በልጅነቷ የምትጋደል ሆነች በቀን በሌሊት ትጾማለች ትጸልያለች፤ወደ ደናግል ገዳም እየሄደችም ታገለግላቸው ነበር፤ የአባቷን ቤት ምግብ ትታ የመነኮሳይያቱን ደረቅ ምግብ ትመገብ ነበር፤ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ ወላጆቿ ሊድሯት አሰቡ የወርቅ የብር ልብሶች፤ ጌጠችና ሽልማቶችን አዘጋጁላት፤ እርሷ ግን ወደ እናቷ ቀርባእማዬ ከደናግሉ ገዳም ሄጄ ተባርኬ ልመለስ እሻለሁአለቻት እናቷምቶሎ ተመለሺ ልጄብላ ከሁለት አገልጋዮቿ ጋር ሰደደቻት፤ቅድ...ስት አክሳኒ አልተመለሰችም በመርከብ ተሳፍራ መጀመሪያ ወደ ደሴተ ቆጵሮስ ከዚያም ወደ እስክንድርያ ሄደች በመንገድ ላይ ሳለች ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በራእይ ተገለጸላት የምትሰራውን ሁሉ ነገራት፤ እርሷም ወደ ሊቀ ጳጳሱ ቴዎፍሎስ ገባች ጸጉሯን ላጭቶ አመነኮሳት፤ ከአባቷ ቤት ይዛው ባመጣችው ወርቅ የቅዱስ እስጢፋኖስን ቤተክርስቲያን አሳነጸችበት፤ ምንም ምን ሳትይዝ ከደናግል ገዳም ገባች፤ ከጥሬ ባቄላ በቀር እሳት የነካውን ምግብ አልተመገበችም ማቅ ለብሳ አመድ ነስንሳ በተጋድሎ ኖረች፤በዛሬዋ ቀንም በክብር አረፈች፤ በዚህ በእረፍቷ ቀን ታላቅ የብርሃን መስቀል ስጋዋ ባረፈበት ቦታ ላይ ታየ በዙሪያውም የሚያበሩ ከዋክብትና የክብር አክሊላት ነበሩ መነኮሳቱ ምን ድንቅ ነገር ነው ብለው ሲቀርቡ መሞቷን ተረዱ ገንዘው እስኪቀብሯት ድረስ መስቀሉ ያበራ ነበር ከዚያ በኃላ ተሰውሯል።ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፤ በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ። መዝ 8410 በረከቷ ይደርብን።

No comments:

Post a Comment