Thursday, February 21, 2013

የካቲት 8



 በዚህች ቀን ክብር ይግባውና ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የአይሁድን ህግ ሊፈጽም ከሁለት የርግብ ጫጩቶች ጋር ወደ ምኩራብ የገባበት ቀን ነው። ሉቃ 222 የአረጋዊ ስምኦንን ታሪክ እዚህ ጋር ያመጡታል። በጥሊሞስ የሚባል ኃያል ንጉስ ነበር ይላል ከገናንነቱ የተነሳ ዓለምን እንደ ገል ቀጥቅጦ እንደ ሰም አቅልጦ የገዛ፤ስሜ ዝንት ዓለም እንዲታወስ ምን ልስራአለ፤ አማካሪዎቹ “46ቱን የብሉይ ኪዳን መጽሐፍትን አስተርጉምአሉት 70 የአይሁድ ሊቃውንትን ሰብስቦ ከዕብራይስጥ ቋንቋ ወደ ጽርዕ ቋንቋ እንዲተረጉሙ አደረገ 70 ሊቃውንት አንዱ ስምኦን ነበር ትንቢተ ኢሳይያስን እንዲተረጉም ደረሰው፤ ሲተረጉም ኢሳ 714 ድንግል በድንግልና ትጸንሳለች ከሚለው ደረሰ፤ እንዴት ድንግል ትጸንሳለች ይህንን ብጽፍ ንጉሱ ከፍ ብሎ አንገቴን ዝቅ ብሎ ባቴን ይቆርጠኝ የለምን ብሎድንግልየሚለውንሴትአለው እንቅልፉን ተኝቶ ሲነቃ ሴት የሚለው ተፍቆድንግልተብሎ ተጽፎ ያገኛል አሁንም ሰርዞሴትብሎ ይጽፋል እስከ ሦስት ጊዜ እንዲሁ ሆነ፤ በሶስተኛው ሊያጠፋው ሲል መልአኩ ተገልጾ አታጥፋው ይህን ሳታይ አትሞትም ብሎታል፤ሉቃ 226 ይህንን ተስፋ ሲጠባበቅ 500 ዓመት በምኩራብ ከአልጋ ተጣብቆ ኖረ። በዛሬዋ ቀን ግን የተነገረው ተስፋ ተፈጸመ ድንግል በድልግልና ወልዳ አየ ማየት ብቻ አይደለም ህጻን የሆነውን እግዚያብሔር በእጁ ታቀፈው እንዲህም አለአይኖቼ ማዳንህን አይተዋል ባሪያህን በሰላም አሰናብተውሉቃ 230 ለእግዚያብሔር ምስጋና ይሁን። ዳግመኛም በዛሬዋ ቀን የገዳመ ሲሐቱ አባ ኤልያስ አረፈ፤ የበቃ ባህታዊ ነው ከዕለታት በአንዱ ቀን ንጉስ ቴዎዶስዮስ አንድ የሚያረጋጋኝ አባት ላኩልኝ ብሎ ወደ ገዳመ ሲሐት መልእክት ይልካል አባቶችም የበቃ አባት ነው ብለው አባ ኤልያስ ይልኩታል፤ ንጉሱ እንዲህ ይለዋል በገድል ነብዩ ኤልያስን እንደምትመስል መነኮሳቱ ነገሩኝ አለው፤ አባ ኤልያስም ቆፍጠን ብሎ ንጉስ ይቅርታ ያድርጉልኝ ነብዩ ኤልያስ ስለደግነቱ ቁራዎች ምግቡን ያመጡለት ነበር (1 ነገ 176) እኔ ግን ምግቤን በጸሐይ ላይ ባሰጣው ቁራ ይዞት ይሄዳል አለው፤ ንጉሱ ሰምቶ ከቃሉ ጣዕም ከአንደበቱ ቅልጥፍና የተነሳ አደነቀ ይላል፤ ይህ አባት ወደ ገዳሙ እስኪመለስ ከንጉሱ ማዕድ ምንም ምን አልቀመሰም በተጋድሎ ኖሮ በዛሬዋ ቀን አርፏል፤ዳግመኛም በዛሬዋ ቀን የከበረች እመቤት ቅድስት አመተ ክርስቶስ አረፈች አገሯ ቊስጥንጥንያ ነው፤ባሏ መስፍን ነበር ሲሞት ገንዘቧን ሁሉ ለድሆች ሰጥታ በአንድ ጥልቅ ዋሻ ውስጥ 11 ዓመት በተጋድሎ ኖረች ዘወትር በሰርክ አዕዋፍ የእፅዋት ፍሬ ያመጡላት ነበር፤ ከዕለታት በአንዱ ቀን እንዲህ ሆነ የንጉሱ ግብር ሰብሳቢ በዘመናችን ቋንቋ ግብር የሚተምን ሲዘዋወር ከአንድ ገዳም ይደርሳል ብዙ የእጽዋት ፍሬ ያለበት ዛፍ ያገኛል ይህ የማን ነው ብሎ አበምኔቱን ይጠይቀዋል እኛ አናውቅም አዕዋፍ ዘወትር ከነቅርንጫፉ እየቆረጡ ሲበሩ እንመለከታለን ራሳቸው ግን አይበሉትም ይህ ሁሌም ያስደንቀናል አሉት፤ አዕዋፉ የሚበሩበትን አቅጣጫ ተከትለው ጉዞ ጀመሩ ከብዙ ድካም በኋላ ወለተ ክርስቶስ ካለችበት ዋሻ ደረሱ ገብተው በረከቷን ተቀበሉ ለአበምኔቱ ታሪኳን ነገረችው እርሱም ጻፈው በበነጋው አረፈች በታላቅ ክብር በብዙ ዝማሬ ቀበሯት፤ ለእግዚያብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ከቅዱሳኑ በረከት ያሳርፈን።

No comments:

Post a Comment