Wednesday, July 17, 2013

ሐምሌ 11



በዚህች ቀን መርባስ ከሚባል አገር የሆነ ቅዱስ ዮሐንስ በሰማዕትነት አረፈ፤በመጥምቁ በቅዱስ ዮሐንስ ብስራት ስለተወለደ ወላጆቹ ዮሐንስ ብለው ስም አወጡለት፤ገና ታናሽ ብላቴና እረኛ ሳለ ምሳውን ለተቸገሩ እየሰጠ እስከ ማታ ይጾም ነበር፤በ 18 ዓመቱ ቅስና ተቀበለ፤በታላቅ ተጋድሎም መኖር ጀመረ፤ሀብተ ፈውስ የተሰጠውም አባት ነበር፤ንጉስ ዲዮቅልጥያኖስ በእስክንድርያ ጣኦትን ሲያቆም ስምኦን ከሚባል አጎቱ ጋር በንጉሱ ፊት ቆመው መሰከሩ ጦኦታቱንም ረገሙ በዚህም ብዙ መከራ ተቀብለው በዛሬዋ ቀን በሰማዕትነት አረፉ። በረከታቸው ይደርብን

LIKE >>>
https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን/117298008428339?ref=hl

No comments:

Post a Comment