Saturday, July 20, 2013

ሐምሌ 13


በዚህች ቀን አባ ብስንድዮስ አረፈ፤ ከዕለታት በአንዱ ቀን አንዲት ደዌ የጸናባት ሴት ፈውስን ፈልጋ ወደርሱ መጣች እርሱ ግን ውዳሴ ከንቱ ፈርቶ ሮጠ ተከተለችው መድረስም በተሳናት ጊዜ እግሩ የረገጠውን መሬት አፈር ዘግና በላችው ፈጥናም ከበሽታዋ ተፈወሰች፤ በእንዲህ ያለ ስራ ለብዙ ዘመን በገዳም ተወስኖ ከኖረ በኃላ ቅድስት ስላሴ ተገለጹለት ቤተክርስቲያንን ትመግብ ዘንድ አለህ ብለውም ቁልፍ ሰጡት ቅፍጥ በሚባል አገርም ኤጲስቆጶስ ሆኖ ተሾመ፤ መንጋውን በፍቅር ሲጠብቅ ኖሮ በዛሬዋ ዕለት በክብር አረፈ፤ በረከቱ ይደርብን
LIKE >>>
https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን/117298008428339?ref=hl

No comments:

Post a Comment