Monday, July 22, 2013

ሐምሌ 15




በዚህች ቀን ውዳሴ ማርያምን የደረሰው ኤፍሬም ሶርያዊው አረፈ፡፡ ይህ አባት በከዋክብት ከሚያመልኩ ወገን የነበረ ሲሆን አባቱም የጣኦት ካህን ነበር በኃላ ከእነርሱ ተለይቶ ወጣ የያዕቆብ ዘነጺብ ደቀ መዝሙር ሆኖ ተማረ፤በባስሊዮስ ዘቄሳርያ እጅ ተሾመ፤ቅዱስ ኤፍሬም ዘወትር የእመቤቴ ምስጋናዋ እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደ ባህር አሸዋ በዝቶሊኝ እንደ ልብስ ለብሼው እንደ ምግብም ተመግቤው እያለ ሲመኝ ይኖር ነበር፤ያሹትን መስጠት ለእግዚያብሔር ልማዱ ነውና አቤቱ የጸጋህን ማዕበል አቁምልኝ እስኪል ድረስ 14 ድርሰት እንዲደርስ አደረገው፤ከነዚህም መካከል ዘወትር የምንጸልየው ውዳሴ ማርያም አንዱ ነው፤ቅዱስ ኤፍሬም በንጽህና በቅድስና ኖሮ በዛሬዋ ዕለት በክብር አረፈ፡፡ በረከቱ ይደርብን

No comments:

Post a Comment