Tuesday, July 9, 2013

ነሐሴ 3



 በዚህች ቀን አባ ስምኦን ዘአምድ አረፈ፤በ 6 ዓመቱ አባቱ እረኛ አደረገው፤ እርሱ ግን ቤተክርስቲያን እየሄደ መጽሐፍትን ያደምጥ ነበር በኃላም ጠፈቶ ወደ ገዳም ሄደ መነኮሰ ሰውነቱን በገድል ያስጨንቃት ነበር፤ወገቡ ላይ ያሰረው ገመድ ሰውነቱን ሰርስሮ ወደ ውስጥ ገባ መግልና ደም ቋጠረ መጥፎ ጠረንም አመጣ መነኮሳቱ ተጠየፉት ከገዳምም አባረሩት እግዚያብሔር በህልም ለአበ ምኔቱ ተገለጸለት ወዳጄ ስምኦን በመንግስተ ሰማያት ከእናንተ እጅግ ይበልጣል ከገባበት ፈልጋችሁ አምጡት ብሎ ገሰጸው መነኮሳቱ መብራት ይዘው ፈለጉት ከብዙ ድካም በኃላ ደረቅ ጉድጓድ ወስጥ ከእባቦችና ጊንጦች ጋር አገኙት እግሩ ላይ ወድቀው ይቅርታ ጠየቁት ወደ ገዳማቸውም መለሱት፤ ከዚህ በኃላ ቁመቱ 60 ክንድ የሚሆን የድንጋይ ምሶሶ ላይ ቆሞ ህዝቡን እያስተማረ ብዙ ገቢረ ታአምራትን እያደረገ 12 ዓመት ሌላ የድንጋይ ምሶሶ ላይ እንዲሁ 30 ዓመት ኖረ ብዙ አህዛብን መለሰ፤ በመጨረሻም በዛሬዋ ዕለት በክብር አረፈ በረከቱ ይደርብን፤

No comments:

Post a Comment