Thursday, September 26, 2013

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን



መስከረም 17

የቅድስት ዕሌኒ ባለቤቷ ተርቢኖስ ይባላል፤ በቅድስና ተፋቅረው ነበር የሚኖሩት፤ ተርቢኖስ የሚል ጽሁፍ ያለበት የአንገት ሀብል አሰርቶላት ነበር። ተርቢኖስ ነጋዴ ስለነበር ከጓደኞቹ ጋር በመርከብ ተሳፍረው እሩቅ አገር ሄደው ከ 3 ዓመት በኃላ ይመለሳሉ፤ታዲያ መርከብ ላይ እንዲህ እያሉ ይጫወታሉ፤ እኛስ በሰላም ወደ አገራችን ተመለስን ሚስቶቻችን ግን በሰላም ይጠብቁን ይሆን ሌላ ወንድ ወደውና ለምደው እንዳይጠብቁን አሉ፤ ተርቢኖስ ደግሞ የኔ ሚስት ዕሌኒ ከኔ ሌላ ማንንም አትወድም አትለምድም ይላቸዋል፤ ያንተ ሚስት ከሄዋን ሴቶች ትለያለችን እኔ ሄጄ ወድጃት ወዳኝ ለምጃት ለምዳኝ ብመጣ ምን ትሰጠኛለህ ይለዋል ንብረቴ ሁሉ ላንተ ይሁን ይለዋል በወረታቸው ተወራርደው ይሄዳል፤ የዕሌኒን ገረድ አስጠርቶ 20 ወቄት ወርቅ እሰጥሻለሁ ሁለቱ ብቻ የሚተዋወቁበትን አንድ ነገር ስጪኝ ይላታል፤ እርሷም እሺ አንተ ነጋዴዎች መጡ የብስ እረገጡ እያልክ ለፍፍ ትለዋለች፤ እንዳለቸው እየዞረ ለፈፈ፤ ገረዷም ወደ ዕሌኒ ቀርባ እመቤቴ ነጋዴዎች መጡ የብስ እረገጡ እየተባለ ነው ገላሽን ታጠቢ ሽቶም ተቀቢ ትላታለች፤ዕሌኒም የአንገት ሀብሏን አስቀምጣ ገላዋን ልትታጠብ ትገባለች ይህን ጊዜ ወስዳ ትሰጠዋለች፤ እርሱም ተርቢኖስ ጋር ሄዶ እየው እፍቅራኝ ውድ ስጦታ ሰጠቺኝ ብሎ ያሳየዋል፤ ሀብሉን ተመለከተው ተርቢኖስ የሚል ፅሁፍ አለበት አመነው፤ አያዘነ 3 ዓመት የደከመበትን ንብረት አስረክቦ እየተበሳጨ ወደ ቤቱ ገባ፤ምን ሆነሃል አለችው ንብረቴን መአበል ወሰደቢኝ አላት፤አትዘን አንተም እኔም ብዙ ወዳጆች አሉን ተበድረን ትነግዳለህ ትለዋለች፤ እርሱም በአሽሙር ልክ ነሽ ያንቺ ወዳጆች ብዙ ናቸው እኔ ግን ወዳጅ የለኝም ደግሞም ባበደርኩበት አገር ተበድሬ በከበርኩበት አገር ተዋርጄ አልኖርም ወደ ሌላ አገር እሄዳለሁ ይላታል፤ ባልና ሚስት አንድ አካል ናቸው ካንተ አልለይም ትለዋለች፤ በመርከብ ተሳፍረው ይሄዳሉ በህሩ መሀል ሲደርሱ ሀብሉን አውጥቶ ያሳያታል ስወድሽ ጠላሺኝ ሳምንሽ ካድሺኝ ይላታል፤ ልታስረዳው ሞከረች አላመናትም በሰጥን ውስጥ አድርጎ ስራሽ ያውጣሽ ብሎ ከባህር ጣላት ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃት ሳጥኑ ተንሳፎ ሄዶ ባህር ዳርቻ ያርፋል አገሩ ሮም ነው ቆንስጣ የተባለ አገር ገዢ ሳጥኑን ሲከፍተው እጅግ የምታምር ሴት አገኘ፤የእየሱስ እናት ማርያም የምትባይው አንቺ ነሽን ይላታል፤እኔ የእርሷ ገረድ ነኝ እንጂ እርሷን አይደለውም፤ ጊዜ ያዋረደኝ ወቅት የጣለኝ ሴት ነኝ ትለዋለች፤ወደ ቤተመንግስቱ ይዟት ገባ፤ በክብር እስከ 6 ወር ጠበቃት ከዚያም አገባት በግብርም አወቃት፤መስከረም 12 ቆስጠንጢኖስ ተወለደ፤ በድብቅ የሃይማኖት ትምህርት አስተማረችው ምክንያቱም ባለቤቷ ጣኦት አምላኪ ነበርና፤ ልጇ በ 25 ዓመቱ በሮም ነገሰ ክርስትናንም ተቀበለ፤ ዕሌኒም የጌታን መስቀል ለማስወጣት እየሩሳሌም ሄደች ከብዙ ልፋት በኃላም መስከረም 16 ደመራ ደምራ መስቀሉን አገኘች፤መስከረም 17 ቁፋሮ ጀመረች ከ 6 ወር ቁፋሮ በኃላ መጋቢት 10 መስቀሉ ወጣ፡፡ ብዙ ተአምራትም ተደርገዋል፤ ለእግዝያብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም ከመስቀሉ በረከት ያሳትፈን፡፡
እሌኒ ቅድስት በ 80 ዓመቷ ጌታችን ተገልጾ ወዳጄ ዕሌኒ ወደ እኔ ልወስድሽ ነው አላት፤ ደነገጠች፤ ምነው ፈራሽ መኖር ትፈልጊያለሽ እንዴ ይላታል፤ እንዳመሰግንህ ትንሽ ብቆይ ትለዋለች፤ ስንት ዓመት ልጨምርልሽ ይላታል፤ ይህማ ባንተ ቸርነት መገባት ይሆን የለም ወይ ትለዋለች፤ 40 ዓመት ጨምሬልሻለሁ ይላታል በ 120 ዓመቷ ግንቦት 9 ቀን አረፈች በረከቷ ይደርብን

LIKE >>> https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን
/117298008428339?ref=hl

መስከረም 15


የሊቀ ዲያቆናት የቀዳሚ ሰማዕት የቅዱስ እስጢፋኖስ ዓመታዊ በዓሉ ነው። ይህም ስጋው የፈለሰበት ነው፤ ነገር ግን አባቶች ባዘዙት መሰረት መስከረም 17 ከመስቀል በዓል ጋር ታቦተ ህጉ ወጥቶ አብሮ ተከብሮ ይውላል። ጥር 1 የእረፍት ቀኑ ነው፤ የተወለደውም በዚሁ ቀን ነው፤ ጥቅምት 17 የተሾመበት ቀን ነው፤ በዓመት እነዚሀ 3ቱ ቀናት ሰማዕቱ በሰፊው የሚዘከርባቸው ቀናት ናቸው። አይሁድ አማጽያን ሰማዕቱን ከገደሉት ከ 300 ዓመት በኃላ እለእስክንድሮስ የሚባል አገሩ ቆስጠንጥንያ ነዋሪነቱ እየሩሳሌም ያደረገ ደገኛ ክርስቲያን በህልሙ ቅዱስ እስጠፋኖስ ተገልጾ ስጋውን እንዲያፈልስ ደጋግሞ ይነግረዋል፤ ስጋውን አስቆፍሮ አስወጣ በዘህም ጊዜ ነፍስን የሚያለመልም ደስ የሚያሰኝ መዓዛ አካባቢውን አወደው፤ በዚህ አላበቃም "ስብሐት ለእግዚያብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብ" እያሉ መለአክት ሲዘምሩ ተሰማ በአካባቢው የነበረው ህዝብ ሰምቶ ተደነቀ፤ ከስጋው ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተደረጉ አይነስውራን አዩ ጎባጦች ቀኑ ለምጻሞችም ነጹ።ከዚህ በኃላ በዚያው በእየሩሳሌም ታላቅ ቤተክርስቲያን አነጹለት ስጋውን በክብር አሳረፉት። ከዓመታት በኃላ በድጋሚ ስጋው ወደ ቆስጠንጥንያ ሄዷል ለዚህም የሚያስገርም ሰፊ ታሪክ አለው። ከሰማዕቱ በረከት ያድለን።

LIKE >>> https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን/117298008428339?ref=hl

Wednesday, September 25, 2013

መስከረም 12

በዚህች ቀን የመላዕክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል መታሰቢያ ነው፤ አባቶቻችን ሊቃውንት ባዘዙት መሰረት ሁሌም ወርሃዊ በዓሉን እናት ቤተክርስቲያን ከዋዜማው ጀምራ በማህሌት በሰዓታት በመዝሙር በኪዳን በቅዳሴ በቁርባን ታከብረዋለች፤ በተመሳሳይ እመቤታችን 21 እንዲሁም በዓለ ወልድ 29 ሁሌም በየወሩ ልክ እንደ ዓመታዊ ክብረ በዓላት በብዙ ምስጋና ተከብረው ነው የሚውሉት።በየወሩ እነዚህ 5 ዕለታት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ልዩ ስፈራ አላቸው። ቅዱስ ፋሲለደስ መስከረም 11 ቀን ሰማዕት እስከሚሆን ድረስ ቅዱስ ሚካኤል ከአጠገቡ ሳይለይ ያጽናናው ያረጋጋው ነበር፤ከሞተም በኃላ ነፍሱን ተቀብሎ አሳረጋት ዘለዓለማዊ ተድላ ደስታ የሚገኝባት ዳግም የማይሞትበት የህይወት አገር አስገባት። በረከቱ ይደርብን። የመስከረም ድርሳነ ሚካኤል

LIKE >>>
https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን/117298008428339?ref=hl

መስከረም 11

በዚህች ቀን ከሮም ከነገስታት ወገን የሆነ ቅዱስ ፋሲለደስ መንግስቱን ክብሩን ትቶ በሰማዕትነት ሞተ።ታሪኩ እንዲህ ነው የሮሙ ንጉስ ኑማርዮስ በውጊያ ሞተ፤ ሮም የሚመራት የሌላት ሆነች፤መኳንንቱ ተሰባስበው ከላይኛው ግብጽ ስሙ አግሪጳዳ የሚባል የፍየሎች እረኛ የሆነ አንድ ሰው አገኙ ኃይለኛና ብርቱ ነበር ባልደራስ አድርገው ሾሙት፤ ከንጉስ ኑማርዮስ ሴት ልጆች አንዲቷ ተመለከተችው፤ ወደደችው አገባችው፤ ስሙንም ዲዮቅልጥያኖስ ብላ አነገሰችው።ከጥቂት ቀናት በኃላ አብያተ ጣኦታት ይከፈቱ አብያተ ክርስቲያናት ይዘጉ ብሎ አዋጀ ነገረ፤ ክርስቲያኖችንም ማሳደድ ጀመረ፤ የፋሲለደስ ልጆች እጅግ ጀብደኞች ነበሩ ዲዮቅልጥያኖስን ሊገድሉት አሰቡ ፋሲለደስ ግን ከለከላቸው ይልቁን በሰማዕትነት ለመሞት እንደተዘጋጀ ነገራቸው፤ ክብር ይግባውና በዲዮቅልጥያኖስ ፊት ቆሞ በጌታችን በእየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ፤ ዲዮቅልጥያኖስ ግን እጅግ ደነገጠ ምክንያቱም ፋሲለደስ ህዝብ የሚወደው ጀግና ከነገስታት ወገን ነበርና፤ ስለዚህም በስውር ወደ ግብጽ ላከው እዚያም እንደደረሰ መኮንኑ ተቀብሎ በርካታ መከራዎችን አደረሰበ በመንኩራኩር፤ በተሳሉ የብረት ዘንጎች፤ በብረት ምጣድ በብረት አልጋ እስተኝተው ከስሩ እሳት አነደዱበት ሌሎች ዘግናኝ መከራዎችን አጸኑበት ሁለት ጊዜ ሞቶ ሁለት ጊዜም ተነሳ በመጨረሻም በዛሬዋ ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ፤ ይህ ሰማእት በአገራችን በስሙ በርካታ አብያተክርስቲያናት 3 ታላላቅ ገዳማት አሉት። በረከቱ ይደርብን። የመስከረም 11 ስንክሳር፤የቅዱሳን ታሪክ
/117298008428339?ref=hl
 

መስከረም 10


ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ጸዴንያ ማርያም ይባላል፡፡ ታሪክ እንዲህ ነው፡- ጸዴንያ በምትባል አገር አንዲት እመቤታችንን አጥብቃ የምትወድ፤እንግዳ የምትቀበል ደገኛ ሴት ነበረች ስሟ ማርታ ነው፤ከዕለታት በአንዱ ቀን ወደ እሩሳሌም የሚሄድ አባ ቴዎድሮስ ሚባል ኢትዮጵያዊ መነኩሴ በቤቷ አደረ፤ሲመለስ የእመቤታችንን ስዕል ገዝቶላት እንዲመጣ ነገረችው፤ቅዱስ ሉቃስ የሳላትን የእመቤታችንን ስዕል ገዝቶላት መጣ፤ይህች ስዕል ስጋን የለበሰች ትመስላላች ከፊቷም ወዝ ሲወጣ ይታይ ነበር ብዙዎችም እየተቀቡ ከበሽታቸው ይፈወሱ ነበር፤ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አድርጋለች፤ለዛች ስዕል የነሐስ መስኮት የሐር መጋረጃ የሚበሩ መቅረዞች ሰርታ በክብር አስቀመጠቻት፤እስከዛሬም አለች፡፡ ከመዲናችን አዲስ አበባ ወጣ ብሎ ቡራዮ ጸዴንያ ማርያም የምትባል ቤተክርስቲያን አለች እጅግ የምታምር በዛሬዋ ቀን ታቦቷ ወጥቶ በደማቁ ተከብሮ ይውላል፤ በዛው አጋጣሚ ቤተክርስቲኑ አጠገብ መንደር መንድረው የሐዋርያትን ዓይነት ኑሮ የሚኖሩ ማህበረሰብ አሉ ማህበረ ጽርአ ጽዮን የሚባሉ ኢንጂነሩም ወዛደሩም ዶክተሩም ሁሉም ገንዘባቸውን በአንድ ላይ እያዋጡ የሚመገቡበት፤ አንድ ዓይነት ኑሮ የሚኖሩበት፤የሚገርም ነው፤በዛሬዋ ቀን ጸበል ጻድቅ አዘጋጅተው ህዝቡን ብሉልን ጠጡልን ይላሉ፡፡ ከእመቤታችን በረከት ያሳትፈን፡፡
ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን የጌታችን ግማደ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ ገባ፤ ታሪኩ እንዲህ ነው የግብጽ ንጉስ ክርስቲያኖችን እንደሚያሰቃይ እና ጳጳሱ አቡነ ሚካኤልን እስርቤት እንደከተታቸው አጼ ዳዊት ሰሙ፤ጦራቸውን ወደ ግብጽ አዘመቱ ሱዳን ሲደርሱ ግን አንድ ነገር ታሰባቸው፤ግብጽን መገደብ የዛኔ ለህይወቱ ሲል ጳጳሱን ይፈታቸዋል ብለው አሰቡ አስበውም አልቀሩ ካርቱም ላይ አባይን ገድበው ወደ በርሃ እንዲፈስ አደረጉት፤በዚህ ጊዜ የግብጽ ንጉስ ጳጳሳሱን ለቀቀ ክርስቲያኖችንም ነጻ አወጣ፤ ይባሱን አጼ ዳዊት ይቅርታ እንዲያደርጉለት የእየሩሳሌም የሮም የአርመንና የቁስጥንጥንያን ነገስታት ማለደ ደብዳቤም በተነ፤ለአጼ ዳዊት ብዙ ወርቅ እጅ መንሻ አቀረበ፤ አጼ ዳዊትም ወርቅ አልፈልግም ይልቅስ የጌታዬን መስቀል ስጠኝ ይሉታል፤ እርሱም መስቀሉን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ነዋያተ ቅድሳትን ጨምሮ ሰጣቸው፤መስከረም 10 ቀን ኢትዮጰያ ገባ፤ ይህ ቀን አጼ መስቀል ተብሎ ይከበራል። መስከረም 21 ግሸን ያረፈበት ቀን ነው።
LIKE >>>
https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን/117298008428339?ref=hl

መስከረም 9

በዚህች ቀን አባ ቢሶር አረፈ። በግብጽ መጺል በሚባል ቦታ አጲስ ቆጶስነት ተሹሞ ህዝቡን በፍቅር የጠበቀ ደገኛ አባት ነበር። እንዲህ ሆነ፤ ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ በሮም ነገሰ ክርስቲያኖችን ማሰቃየት ጀመረ፤ ይህ ወሬ በግብጽ ተሰማ አባ ቢሶርም በሰማዕትነት ለመሞት ወሰነ፤ ህዝቡንም በአውደ ምህርት ላይ ሰብስቦ የእግዚያብሔርን ትዕዛዛት በሙሉ አስተማራቸው እንዲጠብቁት አዘዛቸው ከዚህ በኃላ ወደ ሰማዕትነት አደባባይ ለመሞት እንደሚሄድም ነገራቸው፤ ሁሉም ተላቀሱ በጣም ይወዱት ነበርና እንዳይሄድ አጥብቀው ያዙት ሊያስቀሩት ግን አልቻሉም፤ ከእነርሱ ወጥቶ ሄደ በመኮንኑም ፊት ቆመ፤ በክርስቶስ እንደሚያምን ድምጹን አሰምቶ ተናገረ፤ ጣኦታቱንም ዘለፈ በዚህም ልዩ ልዩ መከራ አደረሱበት ይልቍንም ኤጲስ ቆጶስ መሆኑን ሲያውቁ ስቃዩን አጸኑበት በመጨረሻም በዛሬዋ ዕለት አንገቱን ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ። በረከቱ ይደርብን።
LIKE >>>
https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን/117298008428339?ref=hl

Tuesday, September 17, 2013

መስከረም 8


በዚህች ቀን የነቢያት አለቃ የሆነ የዋህ፤ቅን፤ጻድቅ ሙሴ መታሰቢያው ነው። ከእግዚያብሔር ጋር 570 ቃላትን ተነጋግሯል፤ ከባለሟልነቱ የተነሳ ከዕለታት በአንዱ ቀን እግዚያብሔርን መቼ ነው የምሞተው ብሎ ይጠይቀዋል፤ ዐርብ ቀን ነው ብሎ ይመልስለታ ሙሴም ዐርብ ቀን ሁሌም ራሱን ገንዞ ተዘጋጅቶ ይጠብቃል ሰባት ዓመት አለፈው፤ ከዛ በኃላ ቀኑን ረሳው መዘጋጀቱንም ተወው፤ ነገር ግን ዐርብ ቀን ሁለት መላዕክት በሰው ተመስለው መቃብር ሲቆፍሩ አገኛቸው ምን እየሰራችሁ ነው አላቸው፤ እነሱም ሰው ሞቶብን መቃብር እየቆፈርን ነው አሉት፤ ላግዛችሁ ብሎ ቆፈረላቸው፤ እነሱም የሞተው ሰው አንተን ነው የሚያህለው ውስጥ ግባና ለካልን ይሉታል እርሱም ውስጥ ገብቶ በጀርባው ጋደም አለ ጣር ሳይኖርበት ህማም ሳይሰማው በዛው አሸለበ መላእክት አፈር አልብሰውት ያርጋሉ፤የሙሴ መቃብር እሰካሁን የት እንዳለ አይታወቅም፤ ምነዋ ቢባል እስራኤል በጣም ይወዱት ነበርና ስጋውን እንዳያመልኩት ነው። እንደ ሙሴ ደግ የዋህ ቅን የሆነ ነቢይ እንዳልተነሳና እንደማይነሳ መጽሐፍ በእውነት መሰከረ። ፍቅር እንደ ሙሴ ቸርነት እንደ አብርሃም ጥበብን እንደ ሰሎሞን ስጠን አይደል የምንለው። በረከቱን ያድለን

መስከረም 7


በዛሬዋ ቀን በዴሰተ ጋግራን የተዋህዶ አምድ ወደቀ፤ ይህም አባ ዲዮስቆርስ ነው። የእስክንድርያ 25ኛ ሊቀ ጳጳስ ነው። በሮም ነግሶ የነበረው ፓፓ ሊዮን አንድ ኑፋቄ አመጣ ሁለት ባሕርይ አንድ አካል የሚል በዚያን ወቅት በሮም ነግሰው የነበሩት መርቅያኖስና ሚስቱ ንግስት ብርክያል በዚህ ኑፋቄ ተስማምተው ነበርና በኬልቄዶን ጉባዬ እንዲካሄድ አደረጉ 636 ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት በጉባዬው ተገኙ ዲዮስቆሮስም ተገኘ ሁለት ባህርይ የሚለውን የልዮንን ጦመማር ሰጡት እዘው ጉባይው ፊት ቀደደው ሐዋርያት የመሰረቱት 318ቱ ሊቃውንት የደነገጉት ወልድ ወህድ አንድ አካል አንድ ባህርይ ብለው ነው፤ አንድ አካል ያለው ሁለት ባህርይ የለም ብሎ ከመጽሐፍ እየጠቀሰ አስረዳቸው በነፍስና በስጋ በብረትና በእሳት እየመሰለ አስረዳቸው፤መልስ የሚሰጠው ግን አልነበረም ሁሉም ዝም አሉ፤ አውግዘንሃል ከጉባዬ ውጣልን ብልው አስወጡት። ንግስት ብርክልያ ጉባይው ውሎ እንዴት ነበር ብላ ጠየቀች፤ ሁሉም ሲስማማ ዲዮስቆሮስ ግን አምጾብናል ብለው ነገሮዋት፤ ጥሩልኝ እኔ እመክረዋለሁ አለች አቀረቡላት፤ ለማግባባት ሞከረች ንጉስ የወደደውን ዘመን የወለደውን ተቀብለህ ኑር፤ እምቢ የምትል ከሆነ ግን እናቴ ዮሐንስ አፈወር እንዲሰቃይ እንዳደረች አንተም እንደሱ ትሰቃያለህ አለችው፤ዲዮስቆሮስ ሳቀባት ዮሐንስ አፈወርቅስ የክብር ሞት ሞተ እናትሽ ግን እስካሁን በደይን ትሰቃያለች አላት፤ በዚህ ተቆጥታ አስደበደበችው ጥርሱን አወለቁ ጽህሙን ነጩት፤ የወለቀ ጥርሱን የተነጨ ጽህሙን በፖስታ አድርጎ ዝንቱ ውእቱ ፍሬ ሃይማኖት ይህ የሃይማኖት ፍሬ ነው ብሎ እስክንድርያ ለሚገኙ ምዕመናን ላከላቸው ጥርሱ እንደ ፋና እያበራ ይጠቀሙበት ነበር፤ ከዚህ በኃላ 636ቱ በሙሉ ሁለት ባህርይ ብለው መዝገብ ላይ ፈረሙ ዲዮስቆሮስን ወደ ጋግራን ደሴት በግዞት ይልኩታል እዛ እንደደረሰ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አደረገ በዚያ ደሴት ያሉ ነዋሪዎች አከበሩት ከፍ ከፍም አደረጉት፤ እርሱም በዚያ ደሴት አምስት ድርሳናትን የጻፈ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ህብስቱ ተለውጦ ስጋ ወልደ እግዚያብሔር ጽዋው ተለውጦ ደመ ወልደ እግዚያብሐር የሚሆንበት ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ አንዱ ነው፤ ይህንን አባት ቤተክርስቲያን እምደ ሀይማኖት ብላ ሰይማዋለች በዛሬዋ ቀን በዛው በግዞት ባለበት በጋግራን ደሴት አረፈ። በረከቱ ይደርብን።


LIKE >>>
https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን/117298008428339?ref=hl

Monday, September 16, 2013

የቅድስት አርሴማ ታሪክ በአጭሩ


እናታችን ቅድስት አርሴማ እግዚአብሔርን በቅንነት ያገለግሉ ከነበሩ ከከበሩ ካህናት ወገን ከሆኑ ከቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ቅድስት አትናሲያ በስዕለት ተወለደች፡፡
ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ብሉይን ሐዲስን ተምራ እያነበበች እንዲሁም በተግባር እየተረጎመች ዘወትርም በጸሎት ትተጋ እንደነበር ገድሏ ይተርካል፡፡ በዚህ ዘመን ድርጣድስ የሚባል በአርመን የነገሠ አረማዊ ንጉሥ ለጣዖት የሚሰግድ' ፀሐይንም የሚያመልክ' ክርስቲያኖችንም እኔ ለማመልከው አምላክ መስገድ አለባችሁ በማለት መከራ ያጸናባቸው ነበር፡፡

እናታችን ቅድስት አርሴማም ተጋድሎዋን የጀመረችው የዚህ ጨካኝ ንጉሥ አገልጋይ ወይም ሹም ፳፯ ክርስቲያኖችን እንደልማዱ እየደበደበ' እየገረፈና ልዩ ልዩ ስቃይ እያደረሰባቸው ሲወስዳቸው በማየቷ ነበር፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‘‘ለእነርሱና ለአሕዛብ ምስክር እንዲሆን ስለኔ ወደገዢዎችና ወደ ነገሥታት ትወሰዳላችሁ፡፡’’ (ማቴ. ፲፡፲፮፡፲፱)፡፡ ያለውን በማሰብ ቅድስት አርሴማም ገና በሃያ ዓመቷ የዚህን ዓለም ንጉሥ እኩይ ግብሩን በመንቀፍ ስለ ክርስቶስ ከሚሰቃዩ ወገኖቿ ጋር ግንባር ቀደም በመሆን ትመሰክር ጀመር፡፡ የንጉሡም አገልጋይ በደም ግባቷና በንግግሯ ማማር ተደንቆ በዚች በፈቃዷ ልትሠዋ በወደደች ሴት ምንም ሊያደርግባት ስላልወደደ ወደ ንጉሡ ወደ ድርጣድስ ከሃያ ሰባቱ ክርስቲያኖች ጋር ወሰዳት፡፡ ንጉሡም ብዙ የተነገረላትን ወጣት ሲያይ በውበቷና በንግግሯ ተማርኮ ለዓለማዊ ደስታውና ፍላጎቱ ተመኛት፡፡ ለእርሱም ሙሽራ እንድትሆን ብዙ ወተወታት፡፡ ቅድስት አርሴማ ግን ናቀችው ‘‘እኔ የሰማያዊው ንጉሥ የክርስቶስ ሙሽራ እንጂ የዚህን ዓለም አላፊ ጠፊ የሆነውን ገንዘብና ደስታ የምሻ አይደለሁም፡፡’’ በማለትም መለሰችለት፡፡
ንጉሡም ይህንን ከእርሷ በመስማቱ እጅግ ተቆጣ፤ በመናቁም ተበሳጨ፤ አሽከሮቹንም ጠርቶ በቤተ መንግሥቱ የታሰሩትን አንበሶች እንዲለቀቅባቸው አዘዘ፡፡ አንበሶቹ ግን ይደሰቱ ነበር፡፡ በኋላም ፊታቸውን ወደ ንጉሡና አገልጋዮቹ በማዞር ሩጠው እስኪደበቁ ድረስ አሳደዷቸው፡፡ ንጉሡ ይበልጥ ነደደው ክርስቲያኖቹ በረሃብ እንዲያልቁ እንዲታሰሩ አዘዘ፡፡ እግዚአብሔርም በአምስተኛው ቀን በብርሃን ቤቱን ሞልቶት የሚበሉትን በመሶብ የሚጠጡትን በጽዋ ከሰማይ አወረደላቸው፡፡ ንጉሡም ይህንን በማየቱ ከዚያ አውጥቶ በእሳት ውስጥም አስገባቸው፡፡ ሠለስቱ ደቂቅን የጠበቀ አምላክ እነርሱንም አዳናቸው፡፡ በሌላም በብዙ መንገድ ሊያጠፋቸው እንደሞከረ ገድሏ ይተርካል፡፡ በመጨረሻም ከአማካሪዎቹ ጋር ተማክሮ በሰይፍ እንዲያልቁ ይወስናሉ፡፡
እያንዳንዳቸውን ተራ በተራ ሲሰይፋቸው ቅድስት አርሴማ ለሚሰየፉት ሁሉ የድል አክሊል ከሰማይ ሲወርድላቸው ትመለከት ስለነበር የእርሷን ተራ በጉጉት ትጠብቀው ነበር፡፡ በመደሰቷም እየጸለየች አይዟችሁ ጽኑ ትላቸው ነበር፡፡
በመጨረሻም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጽናቷን ተመልክቶ ቃል ኪዳን ይገባላታል፡፡ ንጉሡም ሌሎቹን አሰይፎ ሲያበቃ ወደሷ ዞሮ በቁጣ እየጮኸ አንቺን እንደ ባልንጀሮችሽ በቀላሉ አልገልሽም ስቃይሽን አጸናብሻለሁ ብሎ ለአገልጋዮቹ ትእዛዝ በመስጠት አይኗን አስወጥቶ በእጇ ያሲዛታል፤ ጡቷን ያስቆርጣል፤ በኋላም አንገቷን ያሰይፋታል በዚሁ ሁኔታ እናታችን ሰማዕትነትን ተቀበለች፡፡
ይህንን ሁሉ መከራ ስለአምላኳ ስትል እራሷን አሳልፋ የሰጠች ድንቅ ሰማዕት ናት፡፡ ነቢዩ ዳዊት በመዝሙሩ ‘‘ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ’’ (መዝ.) እንዳለ ለእናታችንም የገባላት ቃል ኪዳን ‘‘በእኔ ስም አምነሽ የዚህ ዓለም ተድላና ደስታ ሳያታልልሽ አንገትሽን ለሰይፍ ሰጥተሽ ተሰይፈሻል፤ የሰማዕትነት ተጋድሎ ፈጽመሻልና ስምሽን የጠራ፤ በዓልሽን ያከበረ፤ ዝክርሽን የዘከረ፤ ገድልሽን የጻፈና ያጻፈ፤ የሰማና ያሰማም እስከ ፲፪ ትውልድ ድረስ እምርልሻለሁ’’ ሲል ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ በዚህም መሠረት በሷ አማላጅነት አምኖ እገዳሟም ሄዶ በጸሎት የተማጸናት ሁሉ ለችግሩ መፍትሄ አግኝቶ እንደሚመለስ እሙን ነው፡፡ የቅድስት አርሴማ ረድኤት በረከት ጸሎትና ምልጃ ከእኛ ጋር ይኑር፡፡ አሜን አሜን አሜን


አሜን የእናታችን በረከቷ ይደርብን!!!!

LIKE >>>
https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን/117298008428339?ref=hl

Sunday, September 15, 2013

መስከረም 5



በዚህች ቀን የከበረች ቅድስት ሶፍያ በከሃዲው ንጉስ በከላድያኖስ ዘመን ከሁለት ሴት ልጆቿ ጋር በሰማዕትነት አረፈች።ይህች ቅድስት መጀመሪያ ጣኦት አምላኪ ነበረች በኃላም ክርስቶስን ወደ ማምለክ ተመለሰች በዚህም ንጉሱ ተቆጣ ብዙ ጸዋትኦ መከራ አደረሰባት በመጨረሻም አንገቷን ቆረጣት አስከትሎም ልጀቿ በርናባንና አክሳስናን ገደለ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ። ይህ ከሀዲ ንጉስ ሞቶ ደገኛው ንጉስ ቆስጠንጢኖስ በነገሰ ጊዜ ሰጋቸውን አፍልሶ ትልቅ ቤተክርስቲያን ሰርቶላቸዋል።በረከታቸው ይደርብን፡

Thursday, September 12, 2013

የቅድስት ድንግል ማርያም ክብር



የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ክብር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጥቂቱ
ቅድስተ ቅዱሳን ትባላለች። በንጽሕና በቅድስና በክብር የተለየ ደረጃ አላት። ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በቤተክርስቲያን ምስጋና ይቀርብላታል መሠረቱም የእግዚአብሔር ቃል ነው። « ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ። » ሉቃ 1፤28 « ከእግዚአብሔር ተልከው የነገሩሽን የምታምኚ አንቺ ብጽእት ነሽ። » ሉቃ 1፤45 በዚህ መሠረት ቤተ ክርስቲያን እመቤታችንን ብጽእት፤ ፍሥሕት፤ ቅድስት፤ ስብሕት እያለች ታመሰግናታለች። እሷ ራሷ « ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል» እንዳለች ሉቃ 1፤48 ዳዊትም « ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ» ብሏል መዝ 44፤17

እመቤታችን የማማለድ ሥልጣን አላት። እመቤታችን በእግዚአብሔር የተሰጣትን የአማላጅነት ክብር ክርስቲያኖች በማወቅ እመቤታችንን አማልጅን ለምኝልን እያሉ በፀሎት ስሟን ይጠራሉ ወደ እርሷ ይማልዳሉ « የምድር ባለጠጎች አሕዛብ በፊትሽ ይማልላሉ» መዝ 44፤13

መልአኩም እንዲህ አላት «በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን አግኝተሻል» ሉቃ 1፤38 ሞገስ የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ የሚያመለክተው የአማላጅነትን፤ የአስታራቂነትን፤ የባለሟልነትን መብት ነው። ሐዋ ሥራ 7፤45-46 ምልጃዋም በቃና ዘገሊላ ሰርግ ቤት ታይቷል። ዮሐ 2፤1-11

እመቤታችን ስግደት ይገባታል። ቤተ ክርስቲያን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የፀጋ (የአክብሮት) ስግደት እንዲቀርብ ታዛለች ለዚህም መሠረቱ የእግዚአብሔር ቃል ነው። « እግሮቹ በሚቆሙበት ቦታ እንሰግዳለን» መዝ 131፤7 ይህ ጥቅስ አራት ነገሮችን የሚያስተባብር ነው

1ኛ ኢየሩሳሌምን

2ኛ ቤተ ክርስቲያን

3ኛ መስቀልን

4ኛ እመቤታችንን

ለእመቤታችን እግዚአብሔር ሰው ሆኖ በእግሮቹ ምድርን ተመላልሶ ከመቀደሱ በፊት 9ወር ክ5ቀን በማህፀኗ 3 ዓመት ክ6ወር በጀርባዋ በእቅፏ ሆኖ ተመስግኖባታልና « ነገሥታትም አሳዳጊ አባቶች ይሆናሉ እቴጌዎቻችውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል» ኢሳ 49፤23

LIKE >>>
https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን/117298008428339?ref=hl

Wednesday, September 11, 2013

መስከረም 2




በዚህች ቀን መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ አንገቱ የተቆረጠበት ቀን ነው። የ 2 ዓመት ከመንፈቅ ህጻን እያለ ከእናቱ ኤልሳቤጥ ጋር ወደ ሲና በርሃ ተሰደደ፤ በ 7 ዓመቱ እናቱ በርሃ ላይ ሞተችበት በድኗን ታቅፎ አለቀሰ፤ በዚህ ወቅት ጌታችን ህጻን ነበር ለእመቤታችን ዘመድሽ ኤልሳቤጥ አርፋለችና ወደዚያው እንሂድ አላት ዮሴፍና ሶሎሜን ጨምረው ወደ ዮሐንስ መጡ ብቻውንም ሲያለቅስ አገኙት፤ ኤልሳቤጥን ገንዘው ቀበሯት፤ እመቤታችን ለጌታ ዮሐንስን ይዘነው እንሂድ አለችው፤ ጌታም የለም መንገዴን ጠራጊ ነውና እዚሁ በረሃ ነው የሚያድገው አላት። ቅዱስ ዮሐንስ ኤልሳቤጥ ያሰፋችለት የግመል ቆዳ ነበረች እርሷን ለብሶ አንቦጣ የሚባል ቅጠልና የበርሃ ማር እየበላ በብህትውና ኖረ።30 ዓመት ከመንፈቅ ሲሆነው ወደ ዮርዳኖስ ወጣ የጌታን መንገድ አቅኑ እያለ አዋጅ ተናገረ ጌታንም አጠመቀ፤ ጳጉሜ 1 ሄሮድስ እስርቤት ከተተው በዛሬዋ ቀንም አንገቱን ቆረጠው፤ የተቆረጠች አንገቱ ክንፍ አውጥታ 15 ዓመት በደቡብ አረቢያና አካባቢው ሰብካ ሚያዚያ 15 ቀን በክብር አረፈ፤ ደቀመዛሙርቱ ከቀሪው አካሉ ጋር አድርገው ቀበሩት። በረከቱ ይደርብን