Wednesday, September 25, 2013

መስከረም 10


ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ጸዴንያ ማርያም ይባላል፡፡ ታሪክ እንዲህ ነው፡- ጸዴንያ በምትባል አገር አንዲት እመቤታችንን አጥብቃ የምትወድ፤እንግዳ የምትቀበል ደገኛ ሴት ነበረች ስሟ ማርታ ነው፤ከዕለታት በአንዱ ቀን ወደ እሩሳሌም የሚሄድ አባ ቴዎድሮስ ሚባል ኢትዮጵያዊ መነኩሴ በቤቷ አደረ፤ሲመለስ የእመቤታችንን ስዕል ገዝቶላት እንዲመጣ ነገረችው፤ቅዱስ ሉቃስ የሳላትን የእመቤታችንን ስዕል ገዝቶላት መጣ፤ይህች ስዕል ስጋን የለበሰች ትመስላላች ከፊቷም ወዝ ሲወጣ ይታይ ነበር ብዙዎችም እየተቀቡ ከበሽታቸው ይፈወሱ ነበር፤ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አድርጋለች፤ለዛች ስዕል የነሐስ መስኮት የሐር መጋረጃ የሚበሩ መቅረዞች ሰርታ በክብር አስቀመጠቻት፤እስከዛሬም አለች፡፡ ከመዲናችን አዲስ አበባ ወጣ ብሎ ቡራዮ ጸዴንያ ማርያም የምትባል ቤተክርስቲያን አለች እጅግ የምታምር በዛሬዋ ቀን ታቦቷ ወጥቶ በደማቁ ተከብሮ ይውላል፤ በዛው አጋጣሚ ቤተክርስቲኑ አጠገብ መንደር መንድረው የሐዋርያትን ዓይነት ኑሮ የሚኖሩ ማህበረሰብ አሉ ማህበረ ጽርአ ጽዮን የሚባሉ ኢንጂነሩም ወዛደሩም ዶክተሩም ሁሉም ገንዘባቸውን በአንድ ላይ እያዋጡ የሚመገቡበት፤ አንድ ዓይነት ኑሮ የሚኖሩበት፤የሚገርም ነው፤በዛሬዋ ቀን ጸበል ጻድቅ አዘጋጅተው ህዝቡን ብሉልን ጠጡልን ይላሉ፡፡ ከእመቤታችን በረከት ያሳትፈን፡፡
ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን የጌታችን ግማደ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ ገባ፤ ታሪኩ እንዲህ ነው የግብጽ ንጉስ ክርስቲያኖችን እንደሚያሰቃይ እና ጳጳሱ አቡነ ሚካኤልን እስርቤት እንደከተታቸው አጼ ዳዊት ሰሙ፤ጦራቸውን ወደ ግብጽ አዘመቱ ሱዳን ሲደርሱ ግን አንድ ነገር ታሰባቸው፤ግብጽን መገደብ የዛኔ ለህይወቱ ሲል ጳጳሱን ይፈታቸዋል ብለው አሰቡ አስበውም አልቀሩ ካርቱም ላይ አባይን ገድበው ወደ በርሃ እንዲፈስ አደረጉት፤በዚህ ጊዜ የግብጽ ንጉስ ጳጳሳሱን ለቀቀ ክርስቲያኖችንም ነጻ አወጣ፤ ይባሱን አጼ ዳዊት ይቅርታ እንዲያደርጉለት የእየሩሳሌም የሮም የአርመንና የቁስጥንጥንያን ነገስታት ማለደ ደብዳቤም በተነ፤ለአጼ ዳዊት ብዙ ወርቅ እጅ መንሻ አቀረበ፤ አጼ ዳዊትም ወርቅ አልፈልግም ይልቅስ የጌታዬን መስቀል ስጠኝ ይሉታል፤ እርሱም መስቀሉን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ነዋያተ ቅድሳትን ጨምሮ ሰጣቸው፤መስከረም 10 ቀን ኢትዮጰያ ገባ፤ ይህ ቀን አጼ መስቀል ተብሎ ይከበራል። መስከረም 21 ግሸን ያረፈበት ቀን ነው።
LIKE >>>
https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን/117298008428339?ref=hl

No comments:

Post a Comment