Monday, September 2, 2013

ነሐሴ 28



የርዕሰ አበው አብርሃም፤ይስሃቅና ያዕቆብ መታሰቢያቸው ነው። ሐምሌ 28 ታስበው እንዲውሉ ስንክሳሩ ይሰራላቸዋል፤ ነሐሴ 28 ደግሞ የሶስቱም አባቶች የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው፤ ቤተክርስቲያናችን በደማቁ በዓሉን ታከብረዋለች፡፡ የቀደሙ አባቶች አምላከ አብርሃም አምላከ ይስሃቅ አምላከ ያዕቆብ ሲሉ የመጣው መቅስፍት ይመለስ ነበር ጠላትንም ድል ይነሱ ነበር።የእነዚህን አባቶች ገድላቸውን መጀመሪያ ቅዱስ አትናቲዎስ ከሐዋርያት ያገኘውን ጽፎ አቆይቶልናል በኃላም ብጹዕ አቡነ አብርሃም ከግዕዝ ወደ አማርኛ ተርጉመውታል አዘጋጁ ባህታዊ ተክለሚካኤል ናቸው። በአብርሃም ስም በኢትዮጰያ ውስጥ 3 ገዳማት እንዳሉና ዋንኛው ገዳም ከምከም ቃሮዶ በርጥባግ በሚባል ቦታ አቡነ አብርሃም የሚባል ገዳም እንዳለ ይህንን ታቦት ንጉስ ገብረመስቀል ግብጽ እንዳስመጡት ሊቀ ብርሃናት መርቆርዮስ አረጋ የቅዱሳን ታሪክ በሚባል መጽሐፋቸው በሰፊው ያትቱታል፤ አዲስ አበባ ውስጥም 1983 ዓመተ ምህረት ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ብጹአን ጳጳሳት በተገኙበት ታቦቱ  ገብቷል። እግዚያብሔር የአባቶቻችንን በረከት ያድለን።
ገድለ አብርሃም፤የነሐሴ 28 ስንክሳር፤የቅዱሳን ታሪክ

LIKE >>> 
https://www.facebook.com/pages/ተዋህዶ-ሀይማኖታችን/117298008428339?ref=hl

No comments:

Post a Comment