Tuesday, December 3, 2013

ሃያሉ ቅዱስ ገብርዔል



‹‹እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለ አራት ሰዎች አያለው›› ት.ዳን 3፡25

የእግዚአብሔር መልአክ ሃያሉ ቅዱስ ገብርዔል

እግዚአብሔርን የሚያመለኩና የሚገዙ እንዲሁም ለእርሱ ከብርን በመስጠት ያሉ ሁሉ ከነገር እንኳን አንዳች እንደማይጎድላቸው በዘመናት መካከል ተመልክተናል፡፡ ይህም ደግሞ እውነት ነው፡፡ ደግሞም እግዚአብሔር ለሚወዱትየሚሆን ጠባቂ በዙሪያቸው ያቆማል፡፡

እስራኤልላውያን በምርኮ ወደ ባቢሎን ምድር ወረዱ በዚያም በግዞት ኑሮዋቸውን ሲገፎ ሰነበቱ፡፡ የባቢሎንም ምድር ንጉስ የነበረው ናቡ ከደነጾር ቁመቱ ስድሳ ክንድ ወርዱም ስድሳ ክንደ የሆነ ጣዖትን አሰርቶ ዱራ በሚባል ሜዳ ላይ አስቆመው በዚያም አንድ ትህዛዝን አዘዘ በእርሱ ግዛት ስር የሚተዳደሩትን በሙሉ እንደዚህ አላቸው የመለከት ድምጽ በሰማችሁ ጊዜ ለዚህ እኔ ላቆምኩት ምስል ስገዱ የማይሰግድ ግን በዚህ በሚነደው እቶን እሳት ስር ይጣላል አለ፡፡

እንደተባለውም የመለከቱ ድምጽ በተሰማ ጊዜ ሁሉም በግባሩ ተደፍቶ ለቆመው ምስል ሰገደ፡፡ ነገር ግን ከሕዝቡ ምካከል ዎስች ሳይሰግዱ ዝም ብለው ቆሙ፡፡ አስተናባሪዎቹ ግን እንዲሰግዱ ለመኑዋቸው ልጆቹ ግን እንቢ አሏዋቸው፡፡ ይህን ባለማድረጋቸው ወደ ሚነደውና ድምጽም ወደሚያስፈራ እሳት ያማላከቷዋቸው ነገር ግን ጸንተው ቆሙ ልጆቹ ‹‹አምላኩን የሚያውቅ ሕዝብ ይቃወሙታል›› ይላል መጽሐፍ ቅዱስ፡፡

በመሆኑም ልጆቹ ይህን በጽናት ተቃወሙት፡፡ አንሰግድም ብለውም በጽናጽ ቆሙ፡፡ ‹‹የምናመልክው አምላክ ከዚህ ከሚነደው እሳት ያድነናል ባያድነን እንኳን አንተ ላቆምከው ምስል አንሰግድም›› አሉት፡፡

ይህ ዓይነት ነገር ታላቅ እምነት ነው በዚህም ደግሞ ወንጌልን በኦሪት ያስተምሩናል፡፡ ይህም ማለት ‹‹ሳያዩ የሚያምኑ ብጹአን ናቸው›› እነዚህም ልጆች ሳያዩ አመኑ ድግሞም ቁርጥ ያለ መለስ መለሱ፡፡ በቅዱሱ አምላክ መታመን ማለት የእርሱን ጥበቃ የሚሆነውን ታላቅ ድህነት እናገኛለን ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ይላል ‹‹የእግዚአብሔር መላክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል›› መዝ.33፡7፡፡ ይህም በመሆኑ ታዳጊው አምላክ እነርሱን ለመታደግ ሲል መላዕክትን ይልካል፡፡

በዚህም ሁኔታ ንጉሱ ናቡ ከደነጾር በቁጣ እንዲህ አለ ወደ እሳቱ ጨምሩዋቸው አለ፡፡ ወስደውም ወደ እሳቱ ጨመሩዋቸው ነገር ግን በዚህ መሀላል አንድ ትልቅ ነገር ተከሰተ ከሚጣሉት ሶስቱ ልጆች ጋራ ቀድሙ የተገኘው አራተኛው እግዚአብሔር መልአክ ነበር፡፡ እሳቱም መካከል በዝማሬ ተሞሉ፡፡ በዚያም የነበሩት ሁሉ በሆነው ነገር ተገረሙ፡፡ ንጉሱም እንዲህ አለ ‹‹እኔ የተፈቱ በእሳቱ ውስጥ የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለው ›› አለ አራተኛውንም ሲገልጸው ‹‹የአምላክን መልክ ይመስላል›› አለ፡፡

ከሊቃነ መላእክት መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ገብረኤል በገነት አበቦች መካከል የተሾመው የአምላክ ባለሙዋል ነበር መ.ሔኖክ 10፡14፡፡ ከእሳቱ ውስጥ የነበርው፡፡ ለአምላካቸው የሚታመኑትን የሚረዱና የሚያገለግሉ የአምላካችን የእግዚአብሔር አገልጋዮች ቅዱሳን መላእክት ሁሌም ቢሆን እኛን ለመርዳት ይፈጥናሉ፡፡ በመሆኑም መላእክት ፈጣንና ሰውን ለመታደግ የሚተጉ ናቸው፡፡ ‹‹ቅዱሳን መላእክት አፈጣጠራቸው እም ኀበ አልቦ ኀበ ቦ (ካለመኖር ወደ መኖር) አምጥቶ ነው፡ ነገር ግን በግበራቸው በእሳትና በነፋስ ተመስለዋል፡፡ ይህውም እሳት ረቂቅ ነው መላእክትም እንደዚሁ ረቂቃን ናቸው፡ ነፋስ ፈጣን ነው እንደዚሁ መላእክት ፈጣን ናቸው ለተልእኮና እኛን ለመርዳት ፈጣን ናቸው›› (አክሲማሮስ) መዝ. ‹‹መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ አገልጋዮቹን እሳት ነበልባል›› ይላል በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ መላእክት ተፈጥሮ ሲነግረን እንዲሁም በአዲስ ኪዳን ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ እንዲህ ይለናል፡-‹‹ሁሉ መዳንን ይወረሱ ዘንድ ስላላቸው ላመገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን ›› ዕብራውያን 1፡14፡፡ አምላካችን ሁላችንንም ከዚህ ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ሁላችንንም ይጠብቀን፡፡

በተጨማሪም ስለ መላእክት ከመጽሐፍ ቅዱስ ለማንበብ እነዚህን ጥቅሶች ተመለከቱ

ሰውን ይረዳሉ

ዘፍ.16፡7/ ዘፍ.18፡15/ ዘጸ.23፡20/ መሳ6፡11/ 1ኛነገ.19፡5/ 2ኛነገ 6፡15/ ዳን.8፡15-19/ ዳን.3፡17/ ት.ዘካ.1፡12/ ማቴ.18፡10/ሉቃ. 1፡26/ ሉቃ.13፡6/ ዩሐ.20፡11/ ሐዋ.12፡6/ ራዕይ 12፡7/

ስግደት ይገባቸዋል

ዘፍ.19፡1-2/ ዘኁ.22፡31/ ኢያሱ 5፡12/ መሳ.13፡2/ 1ኛ ዜና 21፡1-7/ ዳን.8፡15

LIKE OUR PAGE >>>

No comments:

Post a Comment